Showing posts with label በዓላት. Show all posts
Showing posts with label በዓላት. Show all posts

Monday, September 24, 2012

የመስቀል በዓል ክርስቲያናዊ አከባበር


ዲ/ን አሉላ መብራቱ
    ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ የጌታችን ንዑሳን በዓላት አንዱ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓል ነው፡፡ መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን የመቀደሳችን አርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መንበር ሲሆን አምላካችንን የመንመለከትበት መስታወት ነው።

  ይህ ዕለት ከ300 ዓመታት በላይ ጠፍቶ የነበረውን ቅዱስ መስቀል በንግሥት ዕሌኒ አማካኝነት መገኘቱን የምንዘክርበት በዚህም ደስ የምንሰኝበት ዕለት ነው፡፡ በዓሉ በምን ምክንያት እንደሚከበር ታሪኩን፣ በቅድሰት ቤተ ክርስቲያን ካህናቱና ምእመናን በአንድነት በመሆን እንዴት እንደሚያከብሩት፣ ምእመናን በየአካባቢያቸው በየቤታቸው እንዴት እንደሚያከብሩት ቀጥለን እንመልከት፡፡

Saturday, August 18, 2012

በደብረ ታቦር ክብሩን አየን

     ደብረ ታቦር በግእዝ ቋንቋ ሲሆን የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ (ማቴ 7÷1-8) የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ 
     ቤተ ክርስቲያናችን ከሚከበሩት ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ደብረ ታቦር ነው፡፡ በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን 
በድምቀት ይከበራል፡፡ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምእራባዊ ደቡብ በኩል 10ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ ከባሕር ጠለል 572 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ «ባርቅ የተባለው ጦረኛ ሕዝበ እስራኤልን ይዞ በመዝመት ሲራ የተባለውን የሕዝብ ጠላት በታቦር ድል ነስቶ አሸንፏል» (መሳፍንት.4፡6-14)፡፡ 
     ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡ ክንድህ ከኃይል ጋር ነው ሲል በመዝሙር 88፡12 ስለ ታቦር ተራራ ዘምሯል፡፡ የታቦር ተራራ በገሊላ ከሚገኙ ተራራዎች አንደኛው ሲሆን በዛብሎን ክፍል ውስጥ ለሚኖሩ ልጆች የተሰጠ ቦታ ነው፡፡ 1ኛ ዜና.6፡77 ሐዲስ ኪዳን ግን ረጅም ተራራ ከማለት በስተቀር ታቦር ብሎ ስሙን አይጠራውም፡፡ ሆኖም ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩን እንደገለጠና የዚህም ተራራ ስም ታቦር መሆኑን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ገልጠዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ይህንን ረጅም ተራራ ደብረ ታቦር እያለ በድጓው አስፋፍቶ ጽፏል፡፡ 
     ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ረጅም ተራራ የወጣው ብርሃነ መለኮቱን ክብሩን ለመግለጽ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሴና ከኤልያስ ጋር ተነጋግሮአል፡፡ እነዚህም ሁለት ታላላቅ ሰዎች በበብሉይ ኪዳን ጊዜ ስለ ክርስቶስ ትንቢት የተናገሩ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ያስተማሩ ቅዱሳን ነቢያት ነበሩ፡፡

Monday, June 18, 2012

የሰኔ ቅዱስ ሚካኤል ድርሳን

በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመን በባሕርይ በህልውና አንድ አምላክ ብለን አምነን ሰኔ በባተ በዓሥራ ሁለት ቀን የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ እንዲከበር እንናገራለን ልመናው አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር።
ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት በለጸጋ ጐረቤት ነበረው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር።
ይህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውዬ በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ።

Monday, May 7, 2012

አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤


አንቺ ምሥራቅ ነሽ ልጅሽም እውነተኛ ፀሐይ ነው። /ድጓ/

ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ
     የቤተ ክርስቲያን አባት የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆኖ ስለእመቤታችን ያልዘመረ ፣ያላመሰገነ ያልጻፈ የለም።ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የሚገባውን ንጽጽራዊ ምሳሌ ለሚገባት ወላዲት አምላክ ሰጥቶ አመስጥሮ ዘመረ። እንዲህ በማለት “ አንቺ የብርሃን መውጫ ምሥራቅ ነሽ፤ልጅሽም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን እውነተኛ ፀሐይም ነው።”